የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር በተቋሙ በተለያየ ዘርፍ የሚሰሩ ሰራተኞች “የመሀል ዘመን” በሚል በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ዑማ ሲሆኑ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ፈተናዎች የታለፈበት የሂደት ለውጦችን ደረጃ በደረጃ፤ በሰባት አመታት ውስጥ የታዩ ስኬቶች፤ በአለም አቀፉ ደረጃ የመጡ ለውጦችን ተሞክሮ ፤የሀሰት ትርክትን በእውነት ማርከስ እና የመረጃ አቅምን ማጠናከርን አስመልክተው አብራርተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰነዱ ላይ እንዲሁም ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናኝት አስቻይና አስቻይ ያልሆኑ ነጥቦችን በማንሳት በቡድን በመደራጀት የተወያዩ እና ለችግሮቹ መፍትፈሄ ናቸው ያሏቸውን ነጥቦችንም ጭምር አንስተው ተወያይተዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር ኢንጂነር ታከለ ዑማ የተቋሙ ሰራተኞች የተሟላ ብቃት ፤ ጥንቃቄና ትኩረት ፤ፈጠራና ፍጥነት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፡፡እንደ ሀገር እየተመዘገበ ያለውን ስኬት እዉን ለማድረግ እዚህ ያለው አመራሮች ከታች ያሉ ሰራተኞች ድረስ እንዲደርስ በማድረግ የሚጠበቅባችሁን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባችሁ ብለዋል፡፡
Share this post: on Twitter on Facebook
